ፊም – የሴቶች መብትም የሰው ልጅ መብት ነው

የውጭ ዜጋ ሴቶች እና ቤተሰቦቻቸው የምክር መሥጫ ማዕከል

እርስዎ፣

  • በችግር ላይ ኖት?
  • ድብደባ ደርሶቦታል?
  • ጀርመን አገር በሕጋዊነት ወይስ ያለሕጋዊ ፍቃድ ነዉ የምኖሩት?
  • ምክር፣ መረጃ እና ድጋፍ ይፈልጋሉ?

እኛ ለእርስዎ አለንልዎት ! በሚከተሉት ጉዳዮች ዙሪያ እኛን መጠየቅ ይችላሉ !

  • የመኖሪያና የሥራ ፍቃድን በተመለከተ
  • የሥደት ጥያቄን አስመልክቶ
  • ሥራንና መንግስታዊ የኑሮ ድጋፍን በተመለከተ
  • በትዳር፣ በጘደኝነትንና በቤቴሰብ ዙሪያ
  • ልጆችን ማሳደግና መንከባከብ
  • ከትዳር መለያየትና ፍቺን በተመለከተ
  • ጤንነትና እርጉዝነት
  • የአእምሮ ሕመም፣ በአካል ላይ የደረሰ ጉዳት ካለና አስገድዶ መድፈርን በተመለከተ
  • በቤት ዉስጥ ሃይል የመጠቀም ሁኔታ ካለ
  • የሴት ልጆችን ግርዛት በተመለከተ
  • በትዳርና በጋብቻ ስም ሃይል መጠቀም ካለ
  • አድልኦዊነት ደርስዎቦታል
  • የሙያና የጀርመን ቋንቋ ትምህርትን በተመለከተ

እኛ እንደሚከተለዉ ልንረዳዎት እንችላለን፣

  • መረጃ (እንፎርሜሽን) እና ምክር በናት ቋንቋ በመስጠት
  • ከመንግስታዉ መሥሪያ ቤቶች፣ ሐኪሞች፣ ጠበቆች እንሸኛቹ አለን
  • ባሽቾካይ ሁኔታዎች

ይህ የምክር አገልግሎት የሚሰጠዉ ያለክፊያ በነጻ እና ሚሰጢራዊም ነዉ። እርስዎ ከፈለጉ ማንነትዎን ሳያሳዉቁ አገልግሎታችንን ማግኘት ይችላሉ።

Rahiel Abraha
ሩት አብርሃ
ቴለፎን

+49 (0)69. 87 00 825 – 24
rahiel.abraha@fim-beratungszentrum.de

Information in various Languages